This site uses cookies to store information on your computer. I'm fine with this Cookie information

የእርግዝና መከላከያ

Contraception - Amharic

የእርግዝና መከላከያ
እርግዝናን ለመከላከል፣ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ እስከ ማረጥ ድረስ ያስፈልጋል እና በትክክል ጥቅም ላይ ከዋለ በዘዴው መሰረት ውጤታማ ወይም በጣም ውጤታማ ሊሆን ይችላል። ሰፊ አማራጮች አሉ እና ለእርስዎ የትኛው ዘዴ በተሻለ ሁኔታ እንደሚሰራ እንዲወስኑ ለመርዳት ደስተኞች ነን።

እርግዝና መከላከያ በUK ውስጥ በ NHS አማካኝነት ለሁሉም ሴቶች እና ወንዶች ነጻ ነው።


ሰፊ አማራጮች አሉ እና በሳንዲፎርድ ያሉ ሀኪሞች ወይም ነርሶች የግል ሁኔታዎን ከግምት ውስጥ በማስገባት የትኛው ዘዴ በተሻለ ሁኔታ ለእርስዎ ምቹ እንደሚሆን መወሰን እንድችሉ ለመርዳት ደስተኞች ናቸው።
እንደ አማራጭ ደግሞ፣ ይህንን ከእርስዎ GP ጋር ቢወያዩ የበለጠ ምቾት ሊሰማዎት ይችላል። ብዙ የGP ልምምዶች የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ምክር ይሰጣሉ እና ክኒኖችን፣ ቆዳ ላይ የሚጠገኑ የእርግዝና መከላከያዎች፣ የቀለበት መልክ መከላከያዎች እና መርፌዎችን ያቀርባሉ እና ብዙዎች ጥቅልሎች እና ተከላዎችን ማስገባት ይችላሉ።


በNHS ታላቁ ግላስጎው እና ክላይድ አከባቢ የሚገኙ ከ300 በላይ ወደሚሆኑ መደብሮች በመሄድ ነጻ ኮንዶሞችን ጥንቁቅና በሚስጥር መውሰድ ይችላሉ።


የእኛ የወጣት ሰዎች አገልግሎት እድሜያቸው ከ13 እስከ 17 ለሆነ ሰዎች የእርግዝና መከላከያ አገልግሎትን ይሰጣል።


ሰፋ ያሉ የእርግዝና መከላከያ አማራጮችን እንሰጣለን፣ የሚከተሉትን ጨምሮ፡
• የሆርሞን ጥቅልሎች
• ሆርሞን-የሌላቸው ጥቅልሎች
• ተከላ
• መርፌ
• የተዋሃደ የአፍ ክኒን
• የፕሮጄስቶጂን ብቻ ክኒን
• የተዋሀደ የሆርሞን የቆዳ ላይ መለጠፊያ
• የተዋሀደ የሆርሞን የሴት ብልት ላይ የሚደረግ ቀለበት
• የወንድ እና የሴት ኮንዶሞች
• ዲያፍራምቀዶ ጥገና (ቫሶክቶሚ)
• የድንገተኛ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ


ቀጠሮ እንዴት ይያዛል?

ቀጠሮ ለመያዝ በ 0141 211 8130 ለሳንዲፎርድ ይደውሉ።
የኢንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ካልሆኑ፣ በቀጠሮዎ ላይ አስተርጓሚ እንዲቀርብልዎ መጠየቅ ይችላሉ። ቀጠሮዎን


ሲይዙ የሚፈልጉትን ቋንቋ ይንገሩን እና እናመቻችልዎታለን።
የአስተርጓሚ አገልግሎት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ በ https://www.sandyford.scot/sexualhealth-services/i-need-an-interpreter/ ይገኛል።ሚስጥራዊነትበሚስጥር የሚያዝ አገልግሎት እንሰጣለን እና ያለ እርስዎ ፈቃድ እርስዎን የሚመለከት መለየት የሚችልመረጃን ለማንኛውም ሰው አናጋራም፣ እርስዎ ወይም ሌላ ሰው አደጋ ውስጥ እንዳላችሁ ወይም ጤና ላይ


አደጋ እንዳለ ካመንን በስተቀር። ሲመጡ እውነተኛ ስምዎን እንዲጠቀሙ እናበረታታዎታለን እናበሳንዲፎርድ ውስጥ በኤሌክትሮኒክ መዝገባችን ላይ በሚስጥር ይያዛል።ስለ ወሲባዊ ጤናዎ ከእኛ ጋር መነጋገር
በጉብኝትዎ ወቅት በጣም ጥሩ እንክብካቤ እንደሚያገኙ ለማረጋገጥ፣ የሳንዲፎርድ ሠራተኛ ስለ ህክምና እና
ወሲባዊ ታርክዎ ግላዊ እና ጥንቃቄ የሚሹ ጥያቄዎችን ሊጠይቁ ይችላሉ፣ ለመጨረሻ ጊዜ ወሲባዊ ግንኙነት
መቼ እንዳደረጉ፣ ጥበቃ ያልተደረገለት ወሲብ አድርገው እንደሆነ እና ማንኛውም የበሽታ ምልክቶች ያሉብዎት


እንደሆነ የመሳሰሉትን ዓይነት።
ሠራተኞች እርስዎን ለመወቀስ እዚያ አልተገኙም። ማንኛውም እርስዎ የምናገሩት ነገር አያደነግጠንም ወይም እፍረት አያሰማንም፣ ነገር ግን በተሻለ ሁኔታ እርስዎን መመርመር፣ ማከም እና መደገፍ እንድንችል ሀቁን መናገርይኖርብዎታል። የምትናገሩት ሁሉም ነገር በኤሌክትሮኒክ መዝገብ ሥርዓታችን ላይ በሚስጥር ይያዛል፣ ወደ ሌላአገልግሎት እርስዎን ለመላክ፣ በእርስዎ ፈቃድ፣ መረጃ ማጋራት ካስፈለገን በስተቀር። በጣም አልፈው አልፈውበሚታዩ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ሠራተኞች ለእርስዎ ጥበቃ ሲባል መረጃ ማጋራት ሊያስገልጋቸው ይችላል።የሚመርጡ ከሆነ፣ ወንድ ወይም ሴት የጤና ባለሙያን ለማየት መምረጥ ይችላሉ፣ ነገር ግን ክሊኒኩ ሥራ
የሚበዛበት ከሆነ ከተለመደው በላይ ረጅም ጊዜ መጠበቅ ሊኖርብዎት ይችላል፣ እና ቀጠሮዎን ሲይዙ ይህንን
ሊያሳውቁን ይገባል።


ከመምጣትዎ በፊት ምን ይጠበቃሉ?
የቀጠሮ ርዝመቶች ከ10 ደቂቃዎች እስከ 90 ደቂቃዎች ሊለያዩ ይችላሉ። በቀጠሮዎ ላይ ለፍላጎቶችዎ
እንደምንጨቅ ለማረጋገጥ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ፣ እንደምንሰጠው የአገልግሎት
አካል፣ ለሌላ ቀጠሮ ተመልሰው እንዲመጡ ልንጠይቅዎት እንችላለን።

ቀጠሮ ላይ ሲገኙ ምን ይጠብቃሉ?
ለአስተርጓሚ ጠይቀው ከሆነ፣ በቀጠሮዎ ጊዜ ያገኙዎታል።


እኔ ሲደርስ ምን ይፈጠራል?
ሲደርሱ፣ የቁጥር ካርድ፣ የሚቀርበው አገልግሎት ላይ መረጃ ያካተተ ጥቅል፣ የግል መረጃዎ ምን እንደሚሆን
የሚያብራራ የሚስጥራዊነት ሰነድ፣ እና የምዝገባ ቅጽ በሚሰጥዎ/በምትሰጥዎ እንግዳ ተቀባይ ይቀበላሉ። የእንግዳ
ተቀባዩ/ዋ ለመመዝገብ ተራዎ እስኪደርስ ድረስ እንዲቀመጡ ይጠይቅዎታል/ትጠይቅዎታለች። የምዝገባ ቅጽ
መሙላት ላይ እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ ለእንግዳይ ተቀባይ ማሳወቅ ይችላሉ። እባክዎ ይህንን በቻሉት መጠን
ይሙሉ።


ለምን ያህል ጊዜ መጠበቅ አለብኝ?
በተሰጠዎት የቀጠሮ ጊዜ ተቀራራቢ ላይ እንዲታዩ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። እንዳለመታደል ሆኖ፣ ያ ሳይሆን
የሚቀርባቸው ሁኔታዎች አሉ። ለቀጠሮ መጥተው ለ30 ደቂቃዎች ጠብቀው እና ካልተጠሩ፣ እባክዎ ለእርስዎ
ምን እየተደረገ እንደሆነ መጠየቅ ለሚችል/ለምትችል የእንግዳ መቀበያ አባል ያሳውቁ። በአንድ ጊዜ የሚሰሩ ብዙ
ክሊኒኮች ስላሉን፣ ከእርስዎ ኋላ የደረሰ ሰው በኋላ ሊጠሩ ይችላሉ።


ዘግይቼ ከደረስኩስ?
ታካሚዎች ለቀጠሯቸው ዘግይተው የሚደርሱባቸው አጋጣሚዎች እንዳሉ እናውቃለን። ለቀጠሮዎ ዘግይተው
ከደረሱ፣ ሙሉ የመጀመሪያው የቀጠሮዎ ጊዜን ማክበር እንደምንችል ዋስትና መስጠት አንችልም። ለቀጠሮዎ
ዘግይተው ሲደርሱ፣ የክሊኒክ ቡድን አባል መጥቶ/ታ እንዲያናግርዎ/እንድታናግርዎ እንግዳ ተቀባዩ/ዋ
ያመቻቻል/ታመቻቻለች። አንድ ሰው እስኪገኝ ድረስ መጠበቅ ሊኖርብዎት ይችላል። ለአንዳንድ ክሊኒኮች እና
አሰራሮች ከዘገዩ እርስዎን ለማየት አንችልም። ይህ የሚሆን ከሆነ፣ አማራጭ ቀጠሮን እናመቻችልዎታለን።


በማማከሪያው ጊዜ ማንን አገኛለሁ?
ብዙ አገልግሎቶቻችን የክሊኒካል ባለሙያዎች ቡድን ሠራተኞች አላቸው፣ በአገልግሎቱ መሰረት፣ ሀኪሞች፣
ነርሶች፣ የጤና እንክብካቤ እርዳታ ሰጪዎች፣ አማካሪዎች ወይም የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ሊሆኑ የምችሉትን።
ሁሉም ሠራተኞቻችን፣ እርስዎ ወደ ክሊኒክ ክፍል ሲጠሩ፣ እራሳቸውብ ያስተዋውቃሉ።
ለተለየ የክሊኒክ/የህክምና ባለሙያ ጾታ ምርጫ ካለዎት፣ እባክዎ ቀጠሮዎን ሲይዙ ያሳውቁን። ስንችል ያንን
ጥያቄ ለማክበር እንሞክራለን ነገር ግን ዋስትና መስጠት አንችልም።

ምርመራዎቼ እንዴት ይወሰዳሉ?
በግብረ-ስጋ ግንኙነት ለሚተላለፉ አባላዘር በሽታዎች ምርምራ ከፈለጉ ወይም ማድረግ ከለብዎት፣ የሽንት
ወይም የደም ናሙና ማቅረብ ሊኖርብዎት ይችላል። አንዳንድ ምርመራዎች ከመራቢያ ብልቶችዎ የፈሳሽ ጥርግ
እንዲወሰድ ሊያስፈልጉ ይችላሉ እና፣ ምን ዓይነት ወሲብ እንደፈጸሙ ላይ በመመርኮዝ፣ ከጉሮሮዎ እና ከትልቁ
አንጀት ጫፍ (ፈንጢጣ) ሊወሰድ ይችላል። ይህ ትንሽ ምቹ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን የክሊኒክ ሠራተኞች
እነዚህን ምርመራዎች ለማድረግ የላቀ ስልጠና አላቸው እና በጥሩ እጆች ውስጥ ነው ያሉት። አንዳንድ
ምርመራዎች ሀኪሙ/ሟ ብልቶችዎን እንዲያይ/እንድታይ ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ተመሳሳይ ጾታ ባለው/ላት ሀኪም
መታየት የተሻለ ምቾት የሚሰጥዎ ከሆነ፣ እባክዎ ቀጠሮዎን ሲይይዙ ያሳውቁን።


ልጆችን ይዤ መምጣት እችላለሁ?
ልጆችን ይዞ አለመምጣት በጣም ጥሩ ነው እናም በህንጻው ላይ የልጅ እንክብካቤ አገልግሎቶች የሉም። ከልጅዎ
ጋር መምጣት ካለብዎት፣ እርስዎ በክሊኒክ ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ በመጠባበቂያ አካባቢ ውስጥ
የሚያንከባክቧቸውን ሌላ አዋቂ ይዘው ኑ። ልጆችዎን ከሚታመን አዋቂ ሰው ጋር መተው ከቻሉ በርካታ
የመጫወቻ አካባቢ ያለው ተወዳጅ ፓርክ በመንገዱ አልፎ አለ። ካልሆነ፣ ልጆችዎን ትተው ሌላ ጊዜ ተመልሰው
እንዲመጡ ሊጠየቁ ይችላሉ።